የብልጽግና ፓርቲ 3ኛው ዙር ስልጠና አካል የሆነው የመስክ ጉብኝት በዲላ ከተማ ተካሂዷል
የዲላ ከተማ አስተዳደር መካከለኛ አመራሮች በከተማው በማኑፋክቸሪንግ፣ በከተማ ግብርና፣ በቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ እምርታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ መንግሥት የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በአግባቡ ለመመለስ እያደረገ ያለውን ጥረት ማሳየትና እምርታውን ለማስቀጠል በቁጭት የመሥራት ሞራልን ከፍ ለማድረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ጉብኝቱ የከተማውን የግበርና፣ የማኑፋክቸሪንግና የከተማ ልማት እምርታዎችን ጨምሮ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የእፅዋት ጥበቃና ኢኮ ቱሪዝም ማዕከልን ያካተተ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ጉብኝቱ የፓርቲው መካከለኛ አመራሮች ፀጋን ለይቶ በማልማት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር እንዲመለከቱ ያስቻለና በትብብር ከተሰራ ሁለንተናዊ እምርታን ማስመዝገብ እንደሚቻል ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮች አስረድተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የመካከለኛ አመራር ስልጠና “በመደመር መንግሥት እይታ፤ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ቃል በዲላ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
የብልጽግና ፓርቲ 3ኛው ዙር ስልጠና አካል የሆነው የመስክ ጉብኝት በዲላ ከተማ ተካሂዷል

More Stories
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው
ጥራት ያለው ቡና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የግብርና ቴክኖሎጂን በማስፋት አርሶ አደሩ ለገበያ የሚተርፍ ምርት እያመረተ መሆኑ ተገለጸ