በጎፋ ዞን ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በደንባ ጎፋ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል
በጎፋ ዞን፣ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የብልፅግና ፓርቲ ሰልጣኝ አመራሮች ከስልጠናዉ በተጓዳኝ በወረዳው የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።
“በመደመር መንግስት ዕይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ቃል ሶስተኛው ዙር በሳውላ ከተማ አቅም ግንባታ ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ያሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በደንባ ጎፋ ወረዳ ዶጫ ዳንባላ ቀበሌ በኢንቨስተር ካሌብ ኢያሱ እየተመረተ ያለውን የበቆሎ፣ የሰሊጥና የማሾ ምርጥ ዘር ብዜት ምልከታ አድርገዋል።
የምርጥ ዘር ብዜት ማዕከሉ በዞኑ ጎልቶ የሚታየውን የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር ከመቅረፍ አንጻር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።
ሰልጣኞቹ በወረዳው ዛንጋ ዶርማሌ ቀበሌ የወተት መንደርን እንዲሁም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የዞኑን ብልጽግና ፓርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንጻን ጎብኝተዋል።
በቀበሌው በወተት መንደር የተደራጁ አርሶአደሮች ከአንድ ላም በቀን እስከ 28 ሊትር የወተት ምርት እንደሚያገኙ ገልጸዋል።
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻለው ገላ፤ የመስክ ምልከታዉ ሠልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር ከተግባር ተሞክሮና ከልምድ መማር የሚያስችል ስለሆነ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰልጣኞቹ ያገኙትን ተሞክሮ በመቀመር በአካባቢያቸው ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ሰልጣኝ አመራሮቹ የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት በገባው ቃል መሠረት ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት እያከናወነ እንደሚገኝ መመልከታቸው እጅግ ደስተኛ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል።
ሰልጣኞቹ ከመስክ ምልከታው በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ የሰለጠኑትን ስልጠና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ በመሆኑ የላቀ ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህልና ቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ማጎልበት ይገባል – የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ
በግብርና ትራንስፎርሜሽን ላይ የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ተጨባጭ ለውጥ ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን መንግስት ጤና ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ