በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የተሰጣቸው ሥልጠና በተግባር የታጀበ መሆኑ በቀጣይ ለሚከናወነው ሥራ ውጤታማነት እንደሚያግዝ የዳዉሮ ዞን 3ኛ ዙር ሰልጣኝ አመራሮች ተናገሩ
“በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውና ለመካከለኛ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በሚሰጠው ሥልጠና የዳዉሮ ዞን 3ኛ ዙር ሰልጣኝ አመራሮች በዞኑ እየተሠሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ለ8 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ በነበረው ሥልጠና ተሳታፊ የሆኑ የዳውሮ ዞን መካከለኛ አመራሮች በታርጫ ከተማ አስተዳደር እየተሠራ ያለውን የዳውሮ ባህል ማዕከል ግንባታ፣ ኢትኖግራፊክ ሙዚየም፣ የዶሮ ክላስተር፣ የኮሪደር ልማት፣ የኢት ማዕድን የከሰል ማበልጸጊያ ፋብሪካና ሌሎች የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ተዟዙረው በመጎብኘት ላይ ናቸው።
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሲሰጣቸው የነበረው ስልጠና በተግባር ሲገለጥ ለተሻለ ሥራ እንደሚያነሣሣ ገልጸዋል።
በቀጣይም ከስልጠናው መልስ በየአካባቢያቸው ያሉ ጸጋዎችንና አቅሞችን በመለየት የገጠር ትራንስፎርሜሽን ሽግግር እንዲያደርግና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እንዲታይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ሥልጠናው አቅም የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተማነትን በማስፋፋትና የቱሪዝም ዘርፉን በማሳደግ የኢኮኖሚ አቅም ከፍ በማድረግ ዘርፉን የማነቃቃት ሥራ በተቀናጀ ርብርብ ለመሥራት መዘጋጀታቸውንም አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
በከምባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) ምዝገባ በይፋ መጀመሩን የከተማው ኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደረገ
ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ጨምሮ ለእሳት አደጋ መንስኤ የሚሆኑ የመጠቀሚያ ዕቃዎችን በጥንቃቄ በመጠቀም በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ