በሀሬ ተፋሰስበ በ27 ቀናት ወስጥ 35 ሄክታር መሬት ላይ እርከን ፣ አፈር እቀባና የተለያዩ ዕፅዋት ተከላ መከናወኑ ተገለፀ
በተቀናጀ የመሬትና ውሃ ስራ ላይ ከ13 ሺህ 400 በላይ የአከባቢው ማህበረሰብ እየተሳተፉ እንደሚገኝም ተጠቁሟል ።
በ”ብራይት ” ፕሮጀክት የተከናወኑ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የተገኙ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች ጎብኝተዋል።
ፕሮጀክቱ በአርባምንጭ ከተማ በሃሬ ተፋሰስ የተቀናጀ የመሬትና ውሃ አስተዳደር ስራ የሚበረታቱ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ።
አቶ አለማየሁ አጌና ፣ በዛብህ ባንጋ እና ወ/ሮ ምህረት ገብረ እግዚአብሔር የጫኖ ዶርጋ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ የአፈርና ውሀ ጥበቃው ከዚህ ቀደም በአከባቢውና በአባያ ሀይቅ ላይ ይደርስ የነበረን አደጋ የሚከላከል በመሆኑ ምክንያት ተፋሰሱን እያለሙ እንደሚገኙ ጠቁመዋል ።
ፕሮጀክቱ በአከባቢ ሥነ-ምህዳር ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና ለመቀነስ እየሠራ መሆኑን ያብራሩት ነዋሪዎቹ በሚከናወነው የተፋሰስ ስራ የብራይት ፕሮጀክት የሚደነቅ ስራ በአካባቢው እያከናወነ ይገኛል ብለዋል ።
ለልምድ ልውውጥ አርባምንጭ ከመጡት መካከል ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ አዋሽ ተፋሰስና ከአማራ ክልል አባይ ተፋሰስ የተገኙት አቶ አብርሀም ደርባባና አህመድ ታደለ በተመለከተ ሁሉ መደሰታቸውንና ህብረተሰቡ ለአፈርና ውሀ ጥበቃ የሚያሳየውን መነቃቃት ማድነቃቸውን ገልፀዋል ።
የብራይት ፕሮጀክት አስተባባሪ ይልቃል አንተነህ( ዶ/ር) ፤ በሃሬ ተፋሰስ በ27 ቀናት ወስጥ በዶርጋ፣በእምባ ፣ ጫልባና በሚሌ ንዑሶችና ቀበሌያት ከ35 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ እርከን፣ አፈር እቀባና የተለያዩ ዕፅዋት ተከላ መከናወኑን አውስተዋል ።
እንዲሁም በ358 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ድንጋይ ተሰብስቦ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ መዋሉን የገለፁት አስተባባሪው ፤ በዚሁ ስራ ከ13 ሺህ 400 በላይ ሰዎች መሳተፋቸውን አብራርተዋል ።
ፕሮጀክቱ ከውሃና መሬት ሀብት ማዕከል ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተራቆተውን መሬት መልሶ ማልማት መቻሉን ጠቁመዋል ይልቃል አንተነህ( ዶ/ር)።
በጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊና የተፋሰስ ልማት አስተባባሪ አቶ መስፍን መርጊያ ፕሮጀክቱ በጋሞ ዞን አራት ወረዳዎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እያከናወነ መሆኑን አውስተው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው ተፈጥሮ ከመጠበቅ ባለፈ ምርታማነትን ያሳድጋል እንደሚያሳድ አረጋግጠዋል ።
በኔዘርላንድ ኤምባሲና በአውሮፓ ህብረት የሚደገፈው ፕሮጀክቱ የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶችን ጨምሮ አባይ፣ አዋሽ፣ ኦሞ፣ ጊቤና ተከዜ ተፋሰሶች ላይ የተቀናጀ አፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እየተገበረ ይገኛል ።
በጉብኝት መርሀ ግብሩ ከትግራይ፣ አማራ ፣ከኦሮሚያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ።
ዘጋቢ ፡ ተመኙህ ገረሱ፦ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
አዲሱ የቦንጋ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን የኡፋ እና የውሽውሽ ከተሞችን ያካተተ መሆኑን በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ልማት ዲን አቶ ደጉ በቀለ ገለጹ
የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን እንዲከበር ሲወሰን ዓላማው ብሔር ብሔረሰቦች ባህሎቻቸውን በመለዋወጥ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ሃገራዊ መግባባትን እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው – የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር
20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያዊያን የምክክር ቀን መካሄድ ጀመረ