20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያዊያን የምክክር ቀን መካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ: ሕዳር 28/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያዊያን የምክክር ቀን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው።
20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የሚካሄደው “የኢትዮጵያዊያን የምክክር ቀን” በርካታ እንግዶች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።
በሲምፖዚየሙ ላይ የኢፌዴሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ምሁራን፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የባህል አምባሳደሮችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
ለትምህርት ሥራ ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነትና በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ
በበጀት አመቱ በ71 ሺህ 219 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠት መቻሉ ተገለጸ
የጉራጌ ማህበረሰብ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለትውልድ ለማስተላለፍ የኪነ ጥበብ ዘርፉን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ