የ20ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ክልላዊ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሳጃ ከተማ እደተካሄደ ነዉ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ20ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ክልላዊ የማጠቃለያ ፕሮግራም የክልሉ አንዱ ብዝሃ የክልሉ ማዕከል በሆነዉ በየም ዞን ሳጃ ከተማ እደተካሄደ ነዉ።
“ዴሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረዉ የ20ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በፌደሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት የሚከበር ሲሆን በዓሉ በቀጣይ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ህዳር 29 በሆሳዕና ከተማ ሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ይደርጋል፡፡
በክልላዊ ማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ድልነሳው ታደሰ

More Stories
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የትምህርት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
የህግ ታራሚዎችን አምራች ዜጋ ለማድረግ የስነ-ልቦና ድጋፍና የክህሎት ማጎልበቻ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ