“ዲሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በሀላባ ዞን 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
ህገ-መንግስቱ የኢትዮጵያ ፀጋ የሆነውን ብዝሀነት እንዲከበር፣ መብቶች እንዲከበሩ፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ኀብረ ብሔራዊ አንድነት ስር እንዲሰድ ያስቻለ በመሆኑ የሚያጋጥሙ ጥቃቅን የሆኑ ልዩነቶችን በዲሞክራሲያዊ መግባባት መፍታት ያስፈልጋል ተብሏል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመደከማል ኑሪዬ፣ የዞኑ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች አመራሮች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ምንጭ፡ የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን

More Stories
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው
ጥራት ያለው ቡና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የግብርና ቴክኖሎጂን በማስፋት አርሶ አደሩ ለገበያ የሚተርፍ ምርት እያመረተ መሆኑ ተገለጸ