20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ዞናዊ ማጠቃለያ በተለያዩ መረሀግብሮች በወልቂጤ ከተማ እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፡ ሕዳር 20/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ዴሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ዞናዊ ማጠቃለያ በተለያዩ መረሀግብሮች በወልቂጤ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በዞናዊ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፤ ለ20ኛ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል የእንኳን አደረሰን መልክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም በዓሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች በዓል በመሆኑ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ባህል ቋንቋና ሌሎችም እሴቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ለተግባሩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ፤ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ዞናዊ ማጠቃለያ በሁሉም የዞን መዋቅሮች ከህዳር አንድ ጀምሮ ሲከበር ቆይቶ ዛሬ እንደዞን ከወልቂጤና አበሽጌ ወረዳ አስተዳደሮች በትብብር የማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ የጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳና የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አባላት ተገኝተው ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒት ያቀረቡ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አከናውነዋል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀልን ጨምሮ ሌሎችም የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አማረ መንገሻ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)