የወተት ምርትና ምርታማነት  ለማሳደግ በትኩረት  እየሰራ መሆኑን  በወላይታ  ዞን  የጉኑኖ  ሀሙስ  ከተማ  አስተዳደር  ገለጸ

የወተት ምርትና ምርታማነት  ለማሳደግ በትኩረት  እየሰራ መሆኑን  በወላይታ  ዞን  የጉኑኖ  ሀሙስ  ከተማ  አስተዳደር  ገለጸ

በከብት እርባታ ዘርፍ  የተደራጁ  ማህበራትም ውጤታማነታቸው  እያደገ መምጣቱን  ተናግረዋል።

በእርባታ በዘርፍ  ከተሰማሩት ማህበራት  መካከል  አማዶ የላም እርባታ ማህበር 3 ላሞችን  በ150 ሺህ ብር በመግዛት  ወደ ሥራ  መግባታቸውን  ይናገራሉ።

 ከብቶችን በማዳቀልና  በመግዛት ብዛታቸው  ወደ  20 በማደረስ  የወተት  ምርትና  ምርታማነት   ማሳደጉን የአማዶ የወተት  ላም  ማህበሩ ስብሳቢ ወ/ሮ  ንጋቷ ታደሰ  ተናግረዋል ።

የአማዶ  የወተት  ላም  ማህበር  በየቀኑ   ከመቶ ሊትር በላይ ወተት ምርት  ለከተማ ማህበረሰቦች በመሸጥ በቀን ከ10ሸህ  ብር   በላይ  ከወተት ምርት ገቢ  እንደሚያገኙና  በተጨማሪም በስሩ ከ20 በላይ  ለሥራ አጥ ወጣቶች  የሰራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

በትንሽ  ካፒታል  የተጀመረው የእንስሳት እርባታ በአሁኑ  ሰዓት  ያለው  ካፒታል  ከ10  ሚሊዮን  ብር  በላይ  መሆኑን   ወ/ሮ ንጋቷ ታደሰ  ተናግረዋል።

ሌላኛው  የቤተሰብ  የወተት  ላም  ማህበር፤ ማህበሩ ሲደራጁ  በ80 ሺህ ብር  መነሻ  ካፒታል  የጀመሩት  በአሁኑ  ሰዓት ከአንድ ሚልዮን  ብር  በላይ  መድረሱን  የማህበሩ  ሰብሰቢ  አቶ  ተስፋዩ  ጥላሁን ገልጿል  ።

በጉኑኖ ሐሙስ  ከተማ  አስተዳደር  የግብርና ጽ/ቤት  የእንሰሳት ጤና ህክምና  ባለሙያ ዶ/ር አለሙ አያኖ፤ በከብት እርባታ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የእንስሳት ጤንነት ከመጠበቅ ባሸገር የወተት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዘመናዊ የከብት ዝሪያዎች የማሻሻል ስራዎች  ትኩረት ተስጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገለፀዋል።

በጉኑኖ ሐሙስ  ከተማ አሰተዳደር  የግብርና  ጽ/ቤት  ኃላፊው  አቶ  ማቴዎስ በለጠ በበኩላቸው  የሌማት ትርፋት አካል የሆነው የወተት ምርትና ምርታማነት  መጠን ለማሳደግ እስካሁን ድረስ ዘመናዊ  የከብቶች  ዝርያዎች  የማሻሻል  ስራዎች  መሰራታቸው  ተከትሎ በርካታ ከብቶች በከተማ አስተዳደሩ  መኖራቸውን ነው የገለጹት።

በተጨማሪም የእንስሳት  ጤንነት የመጠበቅ እና መኖ የማመቻቸት  ስራዎች በልዩ ሁኔታ ሲሰሩ መቆየቱ  የተናገሩት ኃላፊው  የከብቶች መኖ  የማመርት  ሥራ   መጀመሩን  ገልጸዋል ።

ዘጋቢ፡- መሰለ ማርካ ከዋካ ቅርንጫፍ