የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በዓል የጋራ ትርክቶችን በማጉላት ልናከብር እንደሚገባ ተገለፀ
በይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በማስመልከት የፓናል ውይይት ተካህዷል።
የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ናዝሬት ዘኬዎስ እንደተናገሩት፣ የሀገራችን ህገ መንግስት ብዝሃነትን ያስተናገደ ሁሉንም ባህሎች፣ ቋንቋዎች እና ሃይማኖቶችንም በእኩልነት መጠቀም እንድንችል ያደረገ በመሆኑ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ስናከብር ህገመንግስቱን በማክበር እና የጋራ ትርክቶችን በማጉላት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
አክለውም 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ስናከብር በሀገር ደረጃ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በህብረተሰቡ መካከል የጋራ ውይይቶችን በማድረግ በተለይም የወጣቶች እና የሴቶች ተሳትፎ በማጠናከር ግንዛቤ ለመፍጠር እየሰተሠራ ነው ብለዋል።
አቶ አበበ ዋቆ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ስነምግባር ኮምሽን ሲሆኑ ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ ህብረተሰቡ አንድነትንና የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን በመገንባት እኩልነት ላይ በተመሰረተ መርህ አብሮ ለመኖር የሚያስችሉንን መሠረት መገንባት ይገባናል ሲሉ አስረድተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሰራዊት አበራ እና ደግፌ ጨበሶ እንደተናገሩት በሚመሩት ቀበሌያት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ በማንሳት በሰላምና እና በፍቅር የመኖር እሴቶችን ለማጎልበት እየሠራን ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:- አብዶ አያላ -ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ እውቀት ጋር በማዋሀድ ጥቅም ላይ ለማዋል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የወተት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሀሙስ ከተማ አስተዳደር ገለጸ
ብዝሀነትን በማስተናገድና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቴን ገለፁ