ብዝሀነትን በማስተናገድና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቴን ገለፁ
20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀንን በማስመልከት በቤንች ሸኮ ዞን ክልላዊ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ 20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ልዩ የሚያደርገው ታላቁን የህዳሴ ግድብ በማጠናቀቅ የማይቻል ነገር እንደሌለ ያሳየንበት እና አያሌ ፕሮጀክቶችን ያጠናቀቅንበት ወቅት ላይ የሚከበር መሆኑ ነው ብለዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም፤ የወደብ ጥያቄያችንን እውን ለማድረግ እንዲሁም የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ሰንቀን የተነሳንበት ወቅት በመሆኑ አንድነታችንን በማጠናከር በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጌታቸው ኬኒ፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበሩ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ትስስርን ማጎልበትና የብሄር ብሄረሰቦች ቱባ ባህሎቻቸውንና እሴቶቻቸውን ለማልማትና ለመጠበቅ ያለመ ነው ብለዋል።
የሀገራችንን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበለጠ የምንፀናበት እና ወደ ከፍታ የምንሸጋገርበት እንዲሁም ከፊታችን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመኖሩ የክልሉ ህዝብ ህብረ ብሄራዊ በሆነ አንድነታቸው ዴሞክራሲ መብቶቻቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙበት በመሆኑ ይህንን ቀን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል አቶ ጌታቸው።
ዴሞክራሲ እና የፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ፤ ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶች የሚል የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በእለቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች የዞን የወረዳ አስተዳዳሪዎች የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች የየብሄረሰቡ የባህል ኪነት ቡድን ተማሪዎች ተገኝተዋል።
20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በነገው እለት በዞኑ ሚዛን አማን ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ዮናስ ወ/ገብርኤል – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ እውቀት ጋር በማዋሀድ ጥቅም ላይ ለማዋል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የወተት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሀሙስ ከተማ አስተዳደር ገለጸ
የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በዓል የጋራ ትርክቶችን በማጉላት ልናከብር እንደሚገባ ተገለፀ