የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስርአተ ትምህርት ክለሳ እና ሀገር በቀል እውቀቶች ልማት ትስስር ላይ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሕዳር 18/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስርአተ ትምህርት ክለሳ እና ሀገር በቀል እውቀቶች ልማት ትስስር ላይ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል እንደገለጹት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሀገር በቀል እውቀት ማማ የሚያሰኛት የበርካታ የሀገረሰብ እውቀቶች ባለቤት ናት።
ሀገር በቀል እውቀትን የሳይንስና የምርምር ውጤት ከሆነው ከዘመናዊ እውቀት ጋር ማዋሀድ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ለሀገር በቀል እውቀቶች ውጤታማነት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በቋንቋዎች ልማት ረገድ በተለይም ከሌሎች የሀገራችን ቋንቋዎች አንጻር እኩል ደረጃ ላይ መድረስ ያልቻለው የጉራጊኛ እና ሌሎችም በቀጠናው ያሉ ቋንቋዎችን ለማልማት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።
የመማር ማስተማር ስራዎችን ለማከናወን የስርአተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ መሆኑና የስርአተ ትምህርት ክለሳው የሀገር በቀል ቅኝት እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
በመድረኩ ከፌደራል፣ ከዩኒቨርሲቲው፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከጉራጌና ከምስራቅ ጉራጌ ዞኖች እና ከቀቤና ልዩ ወረዳ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ መላኩ ንማኒ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ እውቀት ጋር በማዋሀድ ጥቅም ላይ ለማዋል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የወተት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሀሙስ ከተማ አስተዳደር ገለጸ
የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በዓል የጋራ ትርክቶችን በማጉላት ልናከብር እንደሚገባ ተገለፀ