20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሐረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዳውሮ ዞን ምክር ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሐረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዳውሮ ዞን ምክር ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 16/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ምክር ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አንድነትን፣ ፍቅርን፣ ህብራዊነትን እና ሀገርን ለመገንባት የሚረዳ በዓል መሆኑን የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ አየለ ገልጸዋል።

የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በጋራ በቆምንበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ሆነን የምናከብረው በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ወ/ሮ ፀሐይ ተናግረዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየው ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን፥ ህብረ-ብሐራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክር፣ ለኢትዮጵያ ፍቅር እና ሠላም የምናሳይበት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ዘንድሮ ከህዳር ወር ጀምሮ “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በየት/ቤቶች፣ ከቀበሌ እስከ ወረዳ የተከበረ ሲሆን፥ ዛሬ በዞን ደረጃ ማጠቃለያ ሆኖ መከበሩን የዞኑ አስተዳደሪ ገልጸዋል።

በበዓሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክልሉ ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋም ኮምቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አምሳል ንጋቱ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዓሉ ከታች መዋቀር ጀምሮ ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶችን በማሳተፉ የዘንድሮ የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ለየት ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል።

“ህብረ ብሐራዊ ፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ፤ ተግዳሮቶች እና መፋትሄ ሀሳቦች” ሰነድ የቀረበ ሲሆን የበዓሉ ተሳታፊዎች በሰነዱ ፅንስ ሀሳብ፣ ቀጣይ የህብረ-ብሐራዊ አንድታችን ለማጠናከር፣ በልማት፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት አንድነታችንን እናጠናክር ሲሉ ሀሳባቸውን አንስተዋል።

ዘጋቢ፡ እታገኝ ዘነበ – ከዋካ ጣቢያችን