በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት 2ኛ ዙር ሰልጣኝ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በቀቤና ልዩ ወረዳ በመስኖ ልማት እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ስራዎችንና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን እየጎበኙ ነው
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት 2ኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ስልጠና የአመራሩን አቅም በሚገነቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን በክልል ደረጃ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ 2ኛ ዙር ሰልጣኝ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮችም ከስልጠናዉ በተጓዳኝ በልዩ ወረዳው በሩሙጋና በደቀንሺሞላ በመስኖ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችንና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን የመስክ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
በልዩ ወረዳው በመስኖ እየለማ ያለው መሬትና የተሳታፊ አርሶ አደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በዕለቱ በልዩ ወረዳው በሩሙጋ ቀበሌ በ32 ሄክታር መሬት በክላስተር እየለማ ያለ የሽንኩርት ሰብል ተጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ እንዲሁም የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ መኮንን መኔዶ፣ የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሚን በደዊ፣ የልዩ ወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካፉ አረቦን ጨምሮ ሌሎችም የልዩ ወረዳው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሐረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዳውሮ ዞን ምክር ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
በቡና ምርት አሰባሰብ ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ሆነ ሌሎች ጥፋቶች እንዳይጨምሩ በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስራ ከ38ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት መታቀዱ ተገለጸ