በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራ በኮንታ ዞን የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ
የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ሽታ ሻሾ ቀበሌ በህብረት ተደራጀተው የሚሰሩ ሴቶች መካከል ወ/ሮ ጎቶረ ጎደቶና ወ/ሮ ታማኝነሽ ታደሰ በሰጡት አስተያየት ለ6 ተደራጅተው ወደ ተግባር በመግባት የበጋ መስኖ ስንዴ በመዝራት፣ የጓሮ አትክልት በመትከልና የድለባ ስራዎችን በስፋት በመስራት ከአመት ወደ አመት የገቢ ምንጫቸውም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል ።
በህብረት ያልታቀፉ ሴቶችን በአደረጃጀቱ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ በዘንድሮው የምርት ዘመን የተሻለ ምርት ለማግኘት ከወዲሁ እየተዘጋጁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ሌላኛው ከርበላ ባደጉቻ ቀበሌ በህብረት ልማት የሚያለሙ አርሶአደሮች ወ/ሮ መሰለች ማሞና ብርቱካን ብሩ በቡኩላቸው ሴቶች በህብረት በመስራት የኑሮ ደረጃቸውን በማሻሻልና በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲቻሉ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው አደረጃጀቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሱሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
የሴቶች ልማት ህብረት አቅም በማሳደግና አባሎቻቸውን በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ራሳቸውን በመገንባት በየአከባቢያቸው እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የሴቶች ልማት ህብረቶች ያሉባቸውን የአደረጃጀት፣ የአሰራር፣ የክህሎት፣ የአመለካከትና የግብዓት ማነቆዎችን ለመፍታት የስልጠና የምክር አገልግሎት በትኩረት መቀጠል እንዳለበት ተነግሯል፡፡
የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን አበበ የሴቶችን ልማት ህብረት በማጠናከር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ለዘርፉ የተለያዩ ድጋፍ ሥራዎች ትኩረት መሰጠቱ ተናግረዋል፡፡
የሴቶች ልማት ህብረቶቹ የጋራ ዓላማና ግብ ያላቸውና በአንድ ቀበሌ ውስጥ በቅርበት ተደራጅተው ተግባራቶችን በማከናወን በተለይ በግብርና ስራዎች ተጠቃሚ ከመሆንም አልፎ ቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ ለሌሎ የሚተርፍ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል
የሴቶች ልማት ህብረት ግንባር ቀደም እንዲሆኑ በማድረግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ ሞዴል ሴት አርሶአደሮች እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ራሄል ቡልቻ ከዋካ ቅርንጫፍ

More Stories
ለ20ኛ ጊዜ “ዲሞክራሲያዊ አንድነት፤ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለማክበር የጋሞ ዞን ም/ቤት የዝግጅት ሥልጠና እየሰጠ ነው
የእናቶችንና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤና ለማሻሻል እናቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እገዛው የላቀ መሆኑ ተገለፀ
ሀገርን እና ህዝብን በተሻለ ቁመና ማገልገል ይገባል – ርዕሰመስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)