ሀገርን እና ህዝብን በተሻለ ቁመና ማገልገል ይገባል – ርዕሰመስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ሀዋሳ፣ ህዳር 13/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሀገርን እና ህዝብን በተሻለ ቁመና ማገልገል ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰመስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሞድዮ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የመካከለኛና የከፍተኛ አመራር መኮንኖች የምረቃ መርሃ-ግብር ተከናውኗል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ካሣ ባደረጉት ንግግር ፤ ሰልጣኞች መመረቃቸው የክልሉን ፖሊስ ተግባራት በተሻለ ብቃት ለማከናወን እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በህገ-መንግስት፣ በወንጀል መከላከልና በወታደራዊ ስልጠናዎች እንዲሁም በሌሎች በርካታ ዘርፎች በተሰጡ ስልጠናዎች ብቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ተመራቂዎች ህዝብን በታማኝነት የማገልገልና የህግ የበላይነትን የማስከበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ልምድና ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰመስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ ተመራቂዎቹ የፖሊስ መኮንኖች ህዝብንና መንግስትን ለማገልገል የማዕረግ ሽግግር በመብቃታቸው የ“እንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፖሊስ ፍትህ እንዲሰፍን ቀንና ሌሊት የሚተጋና ለሀገር ሉዓላዊነትና ለብሔራዊ ጥቅም መከበር መስዋዕትነት የሚከፍል የክቡር ሙያ ባለቤት መሆኑን ተናግረዋል።
ሀገርንና ህዝብን በተሻለ ቁመና ለማገልገል እድልና አዲስ እውቀት ያገኙበት መሆኑን ገልጸው ፤ ይህንን እድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል ነው ያሉት።
አሁን ላይ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታዎች ፈጣን ምላሽ መስጠትን የሚፈልጉ መሆናቸውን ርዕሰ-መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በከልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ መሰል ስልጠናዎችን መስጠት የሚቻልበትን አቅምና ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የፖሊስ ሠራዊት አባላት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ተዘዋውረው የሚሰሩበትና ኃላፊነታቸውን የሚወጡበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለሀገራዊ ግዴታዎች ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በስልጠና ጊዜያቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተመራቂዎች የተሸለሙ ሲሆን ፤ በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፥ ዮሐንስ ክፍሌ ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
የእናቶችንና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤና ለማሻሻል እናቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እገዛው የላቀ መሆኑ ተገለፀ
የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በርካታ ማሻሻያዎች ማድረጉን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ
የምርኩዝ እግረኞች