የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ስርጭትን ለመግታት የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ጥሪ አቀረበ
የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስና ጉበት በሽታ መከላከያና መቆጣጠር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዳዊት ፈይሳ በህብረተሰቡ ዘንድ በተፈጠረው መዘናጋት የቫይረሱ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የበሽታው ስርጭት እየጨመረ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዳዊት፤ ይህን ለመግታት የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበቀዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በገበያ ስፍራዎችና በህዝብ መገኛ ስፍራዎች ስለበሽታው አስከፊነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ እየሠሩ መሆናቸውን የገለጹት በመምሪያው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ መከላከል ባለሙያ አቶ አሸናፊ ብርሃኑ ናቸው፡፡
አልኮል አብዝቶ ባለመጠቀም፣ ልቅ ከሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት በመታቀብና ለበሽታው አጋላጭ ከሆኑት ነገሮች እራስን በማቀብ ስርጭቱን ለመግታት የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አቶ አሸናፊ አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ስርጭትን ለመግታት የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ጥሪ አቀረበ

More Stories
የዓለም የስኳር ህመም ቀን በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች እየተከበረ ነው
በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችን በማጠናከር የማህበረሰቡን ሕይወት በዘላቂነት ለማሻሻል በትኩረት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ
ጤናማ፣ ደስተኛ እና አምራች ቤተሰብን ለመፍጠር በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ አሉታዎችን ማረም እንደሚገባ ተገለፀ