የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጠና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መሰጠት ጀመረ

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጠና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መሰጠት ጀመረ

ስልጠናው “በመደመር መንግስት የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ቃል የሚሰጥ ነው፡፡

በመደመር መንግስት እይታ የግብርና፣ የገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉ ርዕሶች ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን የስልጠናውን መነሻ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በቦንጋ ከተማ መሰጠት በጀመረው ስልጠና እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

ዘጋቢ፡ ዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን