የሕዝቡን አዳጊ የልማት ፍላጎት ለማሟላትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አዲስ ተሿሚዎች በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ በአሪ ዞን የደቡብ አሪ ወረዳ ምክር ቤት አባላት ገለፁ

የሕዝቡን አዳጊ የልማት ፍላጎት ለማሟላትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አዲስ ተሿሚዎች በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ በአሪ ዞን የደቡብ አሪ ወረዳ ምክር ቤት አባላት ገለፁ

በአዲሱ የአደረጃጀትና የመዋቅር መመሪያ መሠረት የተለያዩ ሹመቶች በሙሉ ድምፅ የፀደቁበት የምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 13ኛ አመት 8ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በጋዘር ከተማ ተካሂዷል።

የአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አስፋው ዶሪ ለምክር ቤቱ አባላት በደቡብ አሪ ወረዳ የተጀመረውን ልማት ሊያስቀጥሉ ይችላሉ ያሉትን ለወረዳ አስተዳዳሪነት አቶ ገብሬ ባይስማይን፣ ለወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ትንሹ ተክሌን፣ ለረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊነት አቶ ሳሙኤል ጠለቅሲ እንዲሁም ለረዳት የመንግስት ተጠሪ እና የፖለቲካና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊነት አቶ አንደቦ አምታታውን በዕጩነት አቅርበው፤ በምክር ቤቱ አባላት ገንቢ አስተያየት ተሰጥቶ በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ቃለ መሐላ በመፈፀም የሥራና የኃላፊነት ርክክብ ተከናውኗል።

የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ በቁርጠኝነት በመሥራት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን እንዲያስቀጥሉ የሁሉም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የምክር ቤት አባላት አስረድተዋል።

በአስቸኳይ ጉባኤው የአሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዬ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ዶሪ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን