በልማትና በመልካም አስተዳደር የሚነሱ ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት አባላት አስታወቁ።
ምክር ቤቱ ባካሄደው 4ኛ ዙር 13ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ አስተዳደር ያቀረበውን የተለያዩ ሹመቶች የምክር ቤቱ አባላት ተቀብለው በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን አስተዳደሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በጉባኤው ባስተላለፉት መልዕክት ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አንድነትን በማጠናከር ለሁንተናዊ ዕድገት ከመቼውም ይልቅ በትጋት ሊንሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
ዛሬ ሹመት ከተሰጣቸው መካከል አቶ ፀጋዬ ታደሰ የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባኤ ሲሆኑ በተሰጣቸው ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት የወከለውን ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አሁን ያለንበት ወቅት እንደ ዞን የቡና ምርት የሚሰበሰብበት በመሆኑ ህብረተሰቡም ያገኘውን ሀብት በመቆጠብ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ አፌ ጉባኤው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በጉባኤው የተሳተፉ የምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት አዲስ ሹመት ከተሰጣቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከወትሮው ይልቅ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡
የዞኑ አስተዳደሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በጉባኤው የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን አቅርበው የምክር ቤቱ አባላት ገንቢ አስተያየት በመስጠት በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የዞኑ ሕዝብ ከማርበርግ ቫይረስ ራሱን መጠበቅ እንዲችል የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ አሳሰበ
የከተሞች ፎረም የልምድ ልውውጥ የሚደርግበት መድረክ ነው – ተሳታፊዎች
የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቼኳይ ጉባኤ አካሄደ