የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቼኳይ ጉባኤ አካሄደ

የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቼኳይ ጉባኤ አካሄደ

ምክር ቤቱ በነበረው ውሎ የላስካ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና አስተባባሪ አካላትን ሹመት መርምሮ አፅድቋል።

በዚህ መሠረት የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ደሳለኝ የላስካ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው እንዲያገለግሉ አቶ ተመሥገን አዘነን በእጩነት ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አፅድቋል።

የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ተመሥገን አዘነ ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር በዙሪያ ወረዳው የሚስተዋለውን ከፍተኛ የበጀት ዕጥረት ለመቅረፍ ገቢን አሟጦ መሰብሰብና ያለውን ውስን ሀብትም ለታለመለት አላማ ብቻ እንዲውል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በግብርና፣ በጤናና ትምህርት እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊና መልካም አስተዳደር ዘርፎች የታቀዱ ተግባራት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበሩ አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው የአስተባባሪ ኮሚቴ አደረጃጀት አባላት ዝርዝርን ለምክር ቤቱ አቅርበው በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።

ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን