የባስኬቶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

የስራ ከባቢን ምቹና የስራ ተነሻሽነት ከመፍጠር አኳያ ያለው አስተዋዕጾ በቀላሉ የሚገመት አለመሆኑን የተናገሩት የባስኬቶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ታጋይ ኩምሳ÷ የተጀመረው የለውጥ ሥራ ወደ ስር ፍ/ቤቶች እንዲሰፋ ይደረጋል ብለዋል።

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የራሱ ህንፃ መኖሩ የሚያስመሠግን ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እጥረት፣ የድምፅ መቅረጫ ማሽን ያለመኖርና፣ የተሽከርካር እጥረት ተቋሙ ይበልጥ አገልግሎቱን ቀልጣፋ እንዳያደርግ ማነቆ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የፍርድ ቤቱን ደረጃ በማሻሻል ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ውጥን ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ደሳለኝ ጠቁመው÷ ዞኑ በተነሱ ችግሮችና ቀጣይ ማስተካከያ በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ አቅም በፈቀደ ለማስተካከል ጥረት ያደርጋል ብለዋል።

‎ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያ