ብልጽግናን ለማረጋገጥ  የፖሊስ አመራር እና አባላትን  አቅም ማሳደግ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ብልጽግናን ለማረጋገጥ  የፖሊስ አመራር እና አባላትን  አቅም ማሳደግ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ሀዋሳ፣ ህዳር 08/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ብልጽግና ለማረጋገጥ የፖሊስ አመራር እና አባላትን  አቅም ማሳደግ ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተናገሩ፡፡

‎ከጆኦስትራቴጂ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና በሚል መሪ ሀሳብ ለክልሉ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተሰጠ  ይገኛል ።‎

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካ ሀገራት የስልጣኔ ተምሳሌት የነበረችና በጦርነት ወቅትም ሌሎች ሀገራትን የምታግዝ፤ ሌሎች ነፃ የወጡበትን ቀን ሲያከብሩ ኢትዮጵያ ግን የድል ቀኗን የምታከብር ሀገር ናት።‎

‎ስትራቴጂክ አቅማችን የሚመዘነው ከምንም በላይ በሰራነው ልማትና ባስመዘገብነው ድል በመሆኑ የውስጥና የውጪ ጠላትን በመመከት እና ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን ከፍታ እናረጋግጣለን ብለዋል።

የሀሳብ ኩስምና ከነበረበት ሰርቶ የሚያሰራ መሪ በመኖሩ ትልልቅ ፕሮጀክቶች መጀመራቸው እንኳን ሳይታወቅ የሚጠናቀቁበት ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል።‎‎

‎ለኩስምና ካበቁን ፈተናዎች ውስጥ ከነጠላ ትርክቶች በተጨማሪ  የመዋቅር መዳከም እና የመሳሉት ምክንያት በመሆናቸው ሁለንተናዊ ሪፎርም በማድረግ ተቋማትን የማጠናከር ስራ መስራቱን ገልፀዋል።

ከስልጠናው ማግስት የፖሊስ አባሉ ቁመናውን በማደስ ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ በመጠቀም አካባቢውን ከወንጀል ስጋት ነፃ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።

ዘጋቢ ፦ገነት መኮንን-ከአርባምንጭ ጣቢያችን