ህዳር 29 ለሚከበረው የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የአሰልጣኞች ሥልጠናና ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ በካራት ከተማ እየተካሄ ይገኛል

ህዳር 29 ለሚከበረው የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የአሰልጣኞች ሥልጠናና ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ በካራት ከተማ እየተካሄ ይገኛል

‎20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኀብረ ብሔራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካራት ከተማ የአሰልጣኞች ሥልጠናና ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

‎በውይይቱ ላይ የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ዕቅድ ይቀርባል።

‎በመቀጠልም “ዲሞክራሲያዊ የፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ” የሚል ሰነድ የህገ-መንግስት ትርጉም እና አስተምህሮ ዳይሬክቶሬት ተቀዳሚ ዳይሬክተር አቶ ሉቃስ ጅማ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

‎በመድረኩ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳዬ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ የሁሉም ዞኖች፣ አፈ ጉባኤዎች፣ የኮሙኒኬሽ ኃላፊዎች፣ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ስራ አስክያጅ፣ የሴቶችና ወጣቶች ክንፍ እዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ይሳተፋሉ።

‎ዘጋቢ፡ ተዋበች ዳዲ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን