በራሳቸው የሚተማመኑ፣ በሥራ ክቡርነት የሚያምኑ፣ የሙያና ክህሎት ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል መፍጠር ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

በራሳቸው የሚተማመኑ፣ በሥራ ክቡርነት የሚያምኑ፣ የሙያና ክህሎት ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል መፍጠር ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በራሳቸው የሚተማመኑ በሥራ ክቡርነት የሚያምኑ የሙያና ክህሎት ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል የመፍጠር ተግባር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሊሆን እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ በ2018 ዓ.ም ንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

ዶ/ር ነጋሽ ዋገሾ እንደተናገሩት የሥራና ክህሎት ዘርፍ በእውቀትና ክህሎት የሚመራ፣ ኢንዱስትሪውንና የኢንተርፕራይዙን ዘርፍ የሚያሳድጉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ሥራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ፣ቴክኒክና ሙያን ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋራ አቀናጅተው መምራትና፣ ኮሌጆችን በመመዘን የብቃት ደረጃ ማሣደግ ለዘርፉ ትራንስፎርሜሽን ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፍ ዶ/ር አቢይ አንዴሞ÷ አገራችን በምታደርገው ልማታዊ ጉዞ አሁን ካለችበት ደረጃ ወደ ኢንዱስትሪ ምዕራፍ በፍጥነት እያደገች መሆኑን ጠቁመው÷ የሥራና ክዕሎት ዘርፍ የሰለጠነ ብቁ የሰው ኃይል በመፍጠር ኢንዱስትሪ ጉዞ የማሳካት ኃላፊነት እንዳለበት አመላክተዋል።

በክልሉ ባሉ ሃያ የቴክኒክና ሙያ ኮለጆች የሚያሰለጥናቸው ሰልጠኞች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል የመፍጠር ሃላፊነት እየተወጣ ያለና በቀጣይም ለበርካቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የገጠር ግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ ግብርና መካናይዜሽን ማጠናከር፣ ተሞክሮ የሚሆኑ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር፣ ቤተሰብና ማህበረሰብ የማምረት አቅም ማሳደግ እና የኮሌጅ ተመራቂዎች ሥራን መፍጠር የሚችሉ ብቁ ሆነው እንዲወጡ የማድረግ ሥራ ላይ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል።

በቀረበው መወያያ ሰነድ ዙሪያ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ያነሱ ሲሆን በየዘርፍ ባሉ ሥራ ሃላፍዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ።

በመድረኩም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ዶ/ር ነጋሽ ዋገሾ፣ የክልሉ ም/ቤት ዋና አፌ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ፣ በክልሉ በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፍ አልማው ዘውዴ ጨምሮ የክልል የዞኖችና የወረዳዎች የሥራ ሃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ኢያሱ ዶላንጎ – ከዋካ ጣቢያችን