ክህሎት መር ስልጠና በመተግበር በሀገሪቱ ያለውን ፀጋ ተጠቅሞ በትጋት ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለወጣቱ የሚሰጠው ክህሎት መር ስልጠና በሀገሪቱ ያለውን ፀጋ ተጠቅሞ በትጋት ሊሠራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ገለፀ።
መምሪያው የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
ወጣቶችን በየሥራ ዘርፉ ለይቶ የክህሎት ስልጠና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ተቀናጅተው መስጠት እንዲጀምሩ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠር የገደብ ከተማና የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስምምነት ተሰማ እና ተካልኝ በቀለ ተናግረዋል፡፡
የዞኑ ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ጥላሁን በ2018 መጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ውስንነቶች መካከል የመስሪያ ቦታ ከማመቻቸት ፣ በብድር ስርጭትና አመላለስ ዙሪያ ላይ መምከራቸውን አስታውሰዋል፡፡
ወጣቱ የሚሰጠውን ክህሎት መር ስልጠና በመተግበር በሀገሪቱ ያለውን ፀጋ ተጠቅሞ በትጋት ሊሠራ ይገባል ያሉት አቶ ታደለ አሁን ያለንበት ወቅት ቡና የሚሰበሰብት በመሆኑ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር እንደሚፈጸም ጠቁመው ቁጠባ በማሰባሰብ ላይ ትኩረት እንዲደረግ በውይይቱ አቅጣጫ መቀመጡን ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ