አዲሱን የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ

አዲሱን የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በፌደራል የተሻሻለው አዲሱን የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት በማድረግ በክልሉ መሰብሰብ ያለበትን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እንዲቻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በዳውሮ ዞን ገሣ ጫሬ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት ጽ/ቤት በአዲሱ የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ዙርያ ከዞን ገቢዎች መምሪያ ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በቦታው የተገኙት የከተማው ኢኮኖሚ ክላስተር አሰተባባሪ አቶ አየለ አይሳ መንግሥት አስፈላጊ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስና ሀገሪቱን በሁንተናዊ አቅጣጫ መቀየር የሚቻለው ግብር በመሰባሰብ በታማኝነት በመክፈል እንደሆነ ተናግሯል።

አዋጁ እንዲሻሻል የተፈለገበት ዋና ዓላማ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉን የህብረተሰብ ክፍሎች ከግብር ጫና ለማዳን፣ የግብር መሰረቶችን ለማስፋት፣ የግብር ሥርዓት ክፍተቶችን ለማስተካከል እና የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል መሆኑን አቶ አየለ ገልጿል።

የዞኑ ገቢዎች መመሪያ ታክስ ትምህትና ኮሚኒኬሽን ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ አስፋው አራሮ እንደተናገሩት ወቅቱ የሚጠይቀውን የልማት ጥያቄ በዘላቂነት ምላሽ ለመስጠት ወቅቱን የጠበቀ የታክስ አስተዳደር ህጎች ማሻሻል መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል።

ለዚህም ደግሞ ግብርን በታማኝነት፣ በአግባብና በወቅቱ መክፈል አስፈላጊ ስለሆነ ግብር ከፋዮች ግብርን በታማኝነት በመክፈል ለክልሉ፣ ለዞንና ወረዳችን ልማት መፋጠን የበኩላቸውን እንዲወጡ በተሻሻሉ የገቢ ግብር አዋጆች፣ መመሪያና ደንቦችን አስመልክቶ በጊዜ በቂ ግንዛቤን በመጨበጥ ወደ ተግባር መግባት ወሳኝ መሆኑን አቶ አስፋው አብራርተዋል።

በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጁ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱ ሲሆን ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል የሚያርፍበትን የግብር ጫና ለመቀነስ፣ የግብር ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የፍትሃዊ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የግብር መሰረትን ማስፋት እንዲሁም የአነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች የግብር አከፋፈል ስርዓት ቀላል እንዲሆን ማድረግ የአዋጁ መሻሻል ዋነኛ አላማ መሆናቸው አቶ አስፋው አስረድተዋል።

ዘጋቢ: አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን