ይህ የተጠቆመው የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የወባ በሽታ፣ የማህፀን በር ካንሰር እና የጡት ካንሰር መከላከል እና መቆጣጠር ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሀኪሜ አየለ፤ እንደ ሀገር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት እየጨመሩ መምጣታቸውን ገልጸው ለዚህም ምክንያቱ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው የግንዛቤ እጥረት ችግር መሆኑን አንስተዋል።
አክለውም በሽታዎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚሰሩ ሥራዎች ቢኖሩም ወደ ሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ ተደራሽ የማድረግ ሥራ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ዋናቃ፤ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለመጨመርና በሽታዎቹ የሚያስከትሉትን ሞት ለመቀነስ የንቅናቄ መድረክ ማድረግ የሚረዳ መሆኑን አስረድተዋል።
ኃላፊው የጤና ባለሙያዎች የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ከማሳሰባቸውም ባለፈ ሴቶችም የጡት ካንሰርና የማህፀን በር ካንሰር ከሚያስከትለው ሞት ራሳቸውን ለመታደግ ቅድመ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ካለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ካደረጉ ከ22 ሺህ በላይ ሴቶች በ172 ላይ በሽታው መገኘቱን እንዲሁም የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ካደረጉ ከ48 ሺህ በላይ ሴቶች በ6ቱ ላይ የበሽታው ምልክት የታየ መሆኑን አብራርተው ተገቢው የህክምና አገልግሎት መሰጠቱን አቶ ሰይፉ ገልጸዋል።
የጨንቻ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ዘውዱ፤ ሆስፒታሉ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች በተለይም የማህፀን በር ጫፍ እና የጡት ካንሰር ምርመራና ህክምናን በልዩ ትኩረት እያካሄደ ከመሆኑም ባለፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን የጤና ባለሙያዎችን በማስተባበር ጤና ኬላዎች ድረስ ወርዶ እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል።
ሥራ አስኪያጁ አክለውም በሽታዎቹ የሚያስከትሉትን ችግር ለመቀነስ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ አስናቀ ካንኮ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
በሴቶች ላይ የጡትና የማህፀን በር ካንሰር የሚያስከትለውን ሞት ለመቀነስ የካንሰር ቅድመ ምርመራ መደረግና ህክምና መውሰድ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

More Stories
በግሉ የኢንቨስትመንት ልማት ዘርፍ እየታዬ ያለውን መነቃቃት ይበልጥ ለማጎልበት ከመንግስት በኩል የሚጠበቁ ድጋፎች መጠናከር እንዳለባቸው የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አሳሰበ
የትራፊክ አደጋን መከላከል የማህበረሰቡ የሁል ጊዜ ተግባር መሆን እንደሚገባ ተገለፀ
የወጣቱን የኢኮኖሚ አቅም ለመገንባት በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥር ቀረበ