በአገሪቱ የተጀመሩ የልማት ጉዞ እንዲሳለጥ የሠላም ዕሴቶችን አጠናክሮ መያዝ እንደሚገባ ተገለጸ

በአገሪቱ የተጀመሩ የልማት ጉዞ እንዲሳለጥ የሠላም ዕሴቶችን አጠናክሮ መያዝ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 01/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአገሪቱ የተጀመሩ የልማት ጉዞ እንዲሳለጥ የሠላም ዕሴቶችን አጠናክሮ መያዝ እንደሚገባ የጋሞ አባት ሁዱጋ ሳዲቃ ስሜ አሳሰቡ፡፡

ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ባህላዊ የእርቅ ስርዓትን በማጠናከር ለአገር አንድነት መትጋት እንዳለባቸውም ሁዱጋ ሳዲቃ መክረዋል።

ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን የሚናገሩት የጋሞ አባት ሳዲቃ: ሠላምን አጥብቀን ሊንይዘው ይገባል ይላሉ።

በጋሞ ባህል የእርቅ ስነ-ስርዓት ‘ዱቡሻ ወጋ’ የሰፈነው ሠላም ዛሬ የጋሞ ምድር የሠላም ተምሳሌት በመባል እየተወሳ መሆኑ ይበልጥ እንዲሰሩ እንዳነሳሳቸው የሚናገሩት አባት ዛሬ በእጃችን የሚገኘው ሠላም ቀላል መስሎን ሳይታየን አጥብቀን በመያዝ አባቶች አርዓያ ሊሆኑ ይገባል ይላሉ።

ጥቃቅን ልዩነቶችን በማጉላት የተጀመረውን የልማት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ለማናጋት የኃይል አማራጭ የሚያደርጉ አካላት በጦርነት ምክንያት አገር አልባ እየሆኑ ካሉ አገራት ልንማር ይገባል ብለዋል።

የፖለቲካ፣ የሐይማኖት እና ሌሎች ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳ ፍትህን ለማስፈን ሲባል ለሁላችን የጋራ የሆነችውን አገር ለማፍረስ ከታሪካዊ ጠላት ጋር መተባበር የጭካኔ ጥግ በመሆኑ÷ ይሔንን የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው በመቆጠብ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገርን ምርጫቸው እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከትናንት የወረስናቸው ጠቃሚ ያልሆኑ አካሔዶችን በመተው ሠላምና መቻቻል የሰፈነበት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት በአንድነት ዙሪያ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።

ዘጋቢ: ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን