አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ መስጠት እንዳለባቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ መስጠት እንዳለባቸው የሀዲያ ዞን ፍትህ መምሪያ አስገነዘበ።
አግባብነት በሌለው ሁኔታ ተገልጋይን ማጉላላት ለተጠያቂነት የሚዳርግ መሆኑ አመላክቷል።
በሀዲያ ዞን ፍትሕ መምሪያ የሕግ ጥናት ማርቀቅ እና ማስረጽ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ወንድሙ ስነሞ እንደገለፁት÷ መንግስት ሕብረተሰቡ የልማትም ሆነ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ባጠረ ጊዜና ጥራት ባለ መልኩ እንዲያስፈጽም የስራ ዘርፎችን በመቅረጽ ማመቻቸቱን ጠቁመው÷ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ አገልገሎት ሰጭ ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች የተሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው አሳማኝ ያልሆኑ ምክንያቶችን በመፍጠር ባለጉዳዮችን ሲያጉላሉ ይስተዋላል ብለዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ባለጉዳይን በተገቢው መንገድ ያለማስተናገድ ለህጋዊ ቅጣት እንደሚዳርግ አመላክተዋል።
በሙስና የተገኘ ሀብት እንደሚወረስ አዋጁ ይደነግጋል ያሉት አቶ ወንድሙ በማንኛውም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የሚሰሩ ሀላፊዎችም ሆኑ ሠራተኞች የተሰጣቸውን የስራ ሀላፊነት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ሕብረተሰቡም ያለአግባብ የሚያጉላሉ አመራሮችንም ሆነ ሠራተኞችን አጋልጦ በመስጠት በሕግ አግባብ ተግባራት እንዲፈፀሙ በሚደረጉ ጥረቶች የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ: ጌታቸው መጮሮ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የጡት ካንሰር የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ቅድመ ምርመራ ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም #ደሬቴድ – ቀጥታ ስርጭት #ዜና24 #ዜና #ደቡብቴቪ
የልማት ሥራዎችን ለማሣካት የሚመደብ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተመላከተ