ሴቶች የቁጠባን ባህል በማዳበር የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ

ሴቶች የቁጠባን ባህል በማዳበር የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ

‎”ትጋት ለላቀ ስኬት!” በሚል መሪ ቃል የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዞን ማዕከል ፐብሊክ ሰርቫንት የሶስቱም ዘርፍ ህብረት የ2018 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

‎በጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በልማት ስራዎች የሴቶችን ንቁ ተሳትፎ በማሳደግ በሩብ ዓመት አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ማስመዝገባቸውን በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የዞኑ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊና የሴቶች ክንፍ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሊዲያ ከበደ ናቸው፡፡

‎እንደ አካባቢያችን አሁን ያለንበት ወቅት ምርት የሚሰበሰብበትና ገንዘብ የሚገኝበት በመሆኑ ሴቶች የቁጠባን ባህል በማዳበር የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ በትጋት እንዲሠሩ ወ/ሮ ሊዲያ ጠቁመው÷ በአፈፃፀሙ በተሻለ የተመዘገቡትን ይበልጥ ማጠናከርና በውስንነት የተስተዋሉትን ማረም እንደሚገባ ኃላፊዋ አመላክተዋል፡፡

‎የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ የሺወርቅ ጥላሁን እንደገለፁት በሩብ ዓመቱ አፈፃፀም የሴቶች አባላት ኮንፈረንስ በየመዋቅሩ በተደራጀ መልኩ መካሄዱን ገልጸው÷ በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሴቶች አደረጃጀት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑት ወገኖች ደርሰው እንባቸውን በማበስ የበኩላቸውን መወጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡

‎በሩብ ዓመቱ አፈፃፀም በሴቶች መሪነት በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቀሴዎች በርካታ ተግባራት መከናወናቸን የጠቀሱት ወ/ሮ የሺወርቅ በሌማት ትሩፋት ሥራዎች ፣ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናና የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ በንቃት መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

‎ዘጋቢ: ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን