የሳውላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊና ምቹ እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሳውላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊና ምቹ እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።
የኦዲት ግኝቶችንና ያለአግባብ የባከነ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ሀብት እንዲመለሥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
የሳውላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ከመንግስትና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚመደበው በጀት ህጋዊ የአሠራር ሥርዐትን ተከትሎ በወቅቱ ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ለማስቻል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ እሰይ ሰራዊት ገልጸዋል፡፡
በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋና ተቋሙን ለሥራ ምቹ ከማድረግ አኳያ ተጨማሪ የቢሮ ክፍሎች ግንባታ ከማድረግ አንስቶ የክፍያና የግዢ ሰነዶች በአግባቡ ተቀምጠው ለኦዲት ግልጽ እንዲሆኑ ማስቻሉን አስረድተዋል።
የውስጥ ኦዲትን ከማጠናከር አኳያ በሁሉም የሥራ ክፍሎች የኦዲት ባለሙያዎችን በመመደብ ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ያነሱት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ እሰይ ሰራዊት ይህም አሰራሩ ከሌብነት የጸዳ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
ያለ አግባብ የባከነውን የመንግስት ሀብትና 5 ሚሊዮን ብር የኦዲት ግኝት ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ከምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ዘጋቢ :- አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም #ደሬቴድ – ቀጥታ ስርጭት #ዜና24 #ዜና #ደቡብቴቪ
የልማት ሥራዎችን ለማሣካት የሚመደብ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተመላከተ
ሴቶች የቁጠባን ባህል በማዳበር የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ