በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ለመረጃ ባለሙያዎች በመረጃ ዲጂታላይዜሽን ዙሪያ በአርባ ምንጭ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።

‎በትምህርት ሴክተር በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የመረጃ አያያዝ ጉድለት ለመቅረፍ የመረጃ መለዋወጫ ሥርዓቱ ወደ ዲጅታል የመረጃ ሥርዓት በማዘመን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ትክክለኛ እና ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን በመጠቀም በየትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በክልሉ ከሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ 240 የአይሲቲ ባለሙያዎችና የመረጃ ባለሙያዎች ስልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መሰጠቱን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢሳይያስ እንድሪያስ ተናግረዋል።

የተማሪዎችን መረጃ በኦንላይን ተከታትሎ ማንነታቸውን ይበልጥ ለማወቅና ድጋፍ ለማድረግም ይረዳል ያሉት ኃላፊው፥ በመረጃ ማዘመን ሥርዓቱ በየደረጃው ያሉ መረጃዎችን በመተንተን የተሳለጠ መረጃ ለማዳረስም ፋይዳው የጎላ እንደሆነ አክለዋል።

‎ስልጠናው ከወትሮ በተለየ መልኩ መሰጠቱን የሚናገሩት ሠልጣኝ መኮንን ቦሻ ቀደም ሲል በማኑዋል ሥርዓት የሚሞላው መረጃ በኦንላይ መተካቱ የመረጃ ጥራትና ትክክለኛነትን በይበል ይፈጥራል ብለዋል።

‎ሥልጠናው ስከታማና ውጤታማ ሥራዎችን ለመሥራት አቅም ይሆንልናል ያሉት ሌላኛዋ ሠልጣኝ ‎ወ/ሮ ይደነቁ አባቴ ናቸው።


በስልጠናው ላይ በክልሉ ያሉ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የሪጂዮ ፖሊሲ ከተማ ባለሙያዎች፣ የትምህርት ኮሌጅ ዲኖችና ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውም ታውቋል።

ዘጋቢ፡ አበበ ዳባ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን