የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንዲያስችሉ የማድረግ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገለጸ
ሀዋሳ:ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ያሉ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንዲያስችሉ የማድረግ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገለጸ፡፡
የመምሪያው የሥራ ኃላፊዎች በዞኑ በአንሌሞና ሚሻ ወረዳዎች በመኸር እርሻና በአርሶአደር ማሰልጠኛ ተቋማት እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ ምልከታ አድርገዋል።
የሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ኃላፍ አቶ ተሻለ ዮሃንስ እንዳሉት÷ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚያስችሉ ማዕከላት ናቸው ብለዋል።
በዞኑ 240 የአርሶአደር ማሰልጠኛ ተቋማት መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ተሻለ፥ 88 ሄክታር ማሳ በምርጥ ዘር መሸፈኑን ጠቅሰዋል።
የሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፍ ሀብታሙ ታደሰ(ዶ/ር) በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት የሚታየው ሰብል ቁመና በቀሪው ጊዜ በተገቢው ክትትል ከተደረገለት በዘንድሮ ዓመት የተሻለ ምርት እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አርሶ አደሩም በቀጣይ በማሰልጠኛ ተቋሙ የለሙና ውጤታማ የሰብል ዝርያዎችን በራሱ መሬት ላይ በማልማት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ዉጤታማ ሊሆን እንደሚገባም ዶክተር ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡
የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንዲያስችሉ የማድረግ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ዶክተር ሀብታሙ ጠቅሰዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የግብርና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች እንደገለጹት የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ተቋማት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ጉልህ ድርሻ አለቸው ብለዋል።
ዘጋብ፡ ሳምራዊት ያዕቆብ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
ህዝብ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
የሸማቹ መብት በማስከበር የተረጋጋ የንግድ ስራ መፍጠር ይገባል – የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን