ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለአረጋዉያን ያስገነባዉን የመኖሪያ እና እንክብካቤ ማዕከል ስራ አስጀመረ

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለአረጋዉያን ያስገነባዉን የመኖሪያ እና እንክብካቤ ማዕከል ስራ አስጀመረ

ማዕከሉ ለ104 አረጋውያን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ክፍሌ ወልደሚካኤል፤ አረጋዉያን በወጣትነት ዕድሜያቸዉ በተለያዩ የስራ መስኮች ባላቸዉ እዉቀትና ልምድ ሀገራቸዉን በማገልግል አሁን ላለነዉ ትዉልድ አስተላልፈዋል ብለዋል።

የአረጋዉያን እንክብካቤ ሃገራችን ከምታካሂዳቸዉ የማህበራዊ ጥበቃዎች አንዱ መሆኑን በመግለጽ፤ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለሌሎች መንግስታዊና መንግሰታዊ ላልሆኑ ተቋማት አርዓያነት ያለዉ ተግባር መከወኑን ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞችና የአስተዳደር አካላት ከራሳቸዉ ደመወዝ ወርሃዊ ተቆራጭ እያደረጉ ተግባሩን ለዚህ ያበቁት በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ማዕከሉን በእኔነት ስሜት ሊጠብቀዉና ሊንከባከበዉ ይገባል ሲሉ ፕሮፌሰር ክፍሌ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በፕሮግራሙ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አልማዉ ዘዉዴ፣ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደገላ ኤርገኖን ጨምሮ ሌሎችም ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን