ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በቡርጂ ዞን የሶያማ ዙሪያ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ ተጠናቀቀ
ምክር ቤቱ በ5ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት እና የቀረቡለትን ሹመቶች በማፅደቅ ተጠናቋል።
የቡርጂ ዞን ሶያማ ዙሪያ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ እስራኤል ገብሬ፤ በጉባኤው በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የተወያዩበት እንደሆነ ተናግረው ጉባኤው ብዙ ሀሳብ የተወሰደበት ነውም ብለዋል።
በጉባኤው የምክር ቤቱን የ2017 ዓ.ም ቃለ ጉባኤ ላይ ሀሳብ እና እስተያየት ተሰጥቶበት በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን በምክር ቤቱ የተከናወኑ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት በምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዳመነች መሐመድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ጠንካራ ጎኖች እንዲቀጥሉ፣ ደካማ ጎኖቹ ደግሞ ለቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲሰሩ ምክረ ሀሳብ ተመላክቷል።
የሶያማ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አኖ፤ በወረዳው በ2017 በጀት አመት በእያንዳንዱ ሴክተር መስሪያ ቤት የተከናወኑ ተግባራትን ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ከታቀደው እቅድ አንፃር ጥሩ ጅምሮች እንዳሉ አብራርተው፤ ከሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም አንዳንድ የመሰረተ ልማት ስራዎች አንፃር ቀሪ ስራዎችን እንዳሉና ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰሩ እንደሚገባ አንስተዋል።
በቀርበው ሪፖርት ላይ የጉባኤው ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት የሰጡ ሲሆን በተለይ በወረዳው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው የቆዩ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በቂ አለመሆን፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ችግር፣ ከጎረቤት ህዝቦች ጋር በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በትኩረት መስራት የሚሉ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች በስፋት ተነስቶ ከአስፈፃሚ አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
በጉባኤው የሶያማ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሉላ ሾንቃ አማካኝነት ረፖርት ቀርቦ ሀሳብ ተሰጥቶበት በምክር ቤቱ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
በመጨረሻም በጉባኤው የሶያማ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ረቂቅ በጀት በአጠቃላይ 316 ሚሊየን 742 ሺህ 70 ብር ሆኖ ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን በወረዳው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት እውቅና በመስጠት እና የተለያዩ ሹመቶች ለምክር ቤቱ ቀርበው በማፅደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በቡርጂ ዞን የሶያማ ዙሪያ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ ተጠናቀቀ

More Stories
በስብዕና ግንባታ ስራ ላይ በማተኮር በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ገለፀ
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለአረጋዉያን ያስገነባዉን የመኖሪያ እና እንክብካቤ ማዕከል ስራ አስጀመረ
የትምህርት ዘርፍ መጠናከር ሀገሪቱ ወደ አዲስ የስልጣኔ ማማ ለመድረስ ለምታደርገው ጉዞ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ