በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ገለፀ።

‎መምሪያው የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት አካሂዷል።

‎በወቅቱ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይሶጸ ህሎታ እንዳሉት፥ ክልሉ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባርን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡

‎በክልሉ በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ቢሮው የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጥቀስ የባድርሻ አካላት ትብብር እና ድጋፍም በተገቢው ሊከወን የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለፁት።

‎የዲላ ከተማ ምክትል ከንቲባና ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ በየነ በ2018 መጀሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች ቋሚና ጊዜያዊ ሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል።

‎ኃላፊው አክለውም የሥራ ዕድል ከተፈጠረባቸው ዘርፎች ለሚ ኩራ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ኮሪደር ልማት፣ የከተማ ግብርናና አገልግሎት ዘርፎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

‎በተለያዩ ጊዜያት ተወስደው ያልተመለሱ ውዝፍ ብድሮችን የማስመለስ ተግባርን በትኩረት በማከናወን ተጨማሪ ብድር ለማመቻቸት በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

‎ለሥራ ፈጣሪዎች ምቹ የብድር አቅርቦት እያከናወነ መሆኑን የገለጹት የኦሞ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው በራሶ፥ በዲላ ከተማ በተያዘው በጀት ዓመቱ ለሥራ ፈጣሪ 11 ማህበራት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መሰራጨቱን አስታውቀዋል።

‎በወቅቱ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በከተማው በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

‎ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን