በመኸር እርሻ የተዘሩ ሰብሎችን ከአረምና ተባይ የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) አርሶ አደሩ በምርት ዘመኑ በመኸር እርሻ የተዘሩ ሰብሎችን ከአረምና ተባይ የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የቡርጂ ዞን ሶያማ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት።
በወረዳው የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን በራስ አቅም ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።
በቡርጂ ዞን ሶያማ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል እና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ለማ ጫቶ እንደገለፁት፥ በ2017/18 የምርት ዘመን በመኸር እርሻ በጤፍ፣ በቡራቡርጄ ቦሎቄ እና በሌሎችም ሰብሎች በዘር ከተሸፈነው 74 ሺህ 179 ሄክታር መሬት ከ9 ሚሊዮን 199 ሺህ 321 ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል፡፡
በወረዳው ሊዘራ ከታቀደው ሰብሎች መካከል በብዛት የተሸፈነው በቡራቡርጄ ቦሎቄ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ለማ፥ የአረምና ተባይ ቁጥጥር ሥራውን የቤተሰብን ጉልበት በመጠቀም በእጅ ማከናወን መቻሉን አስታውቀዋል።
በዚህም 49 ሺህ 639 ሄክታር ማሳ ሙሉ በሙሉ የታረመ ሲሆን ሌሎችም እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እና በመሳሰሉት ደግሞ በኬሚካል አረም የመቆጣጠር ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።
ከተባይ ቁጥጥርና የመከላከል ሥራ ጋር ተያይዞ በወረዳው በተለይም በበቆሎ ምርት ላይ “አሜሪካን ፎሊ ዎርም” የተባለ ተባይ ተከስቶ እንደነበር ያስተወሱት አቶ ለማ፥ በመድኃኒት እና በባህላዊ መንገድ የመቆጣጠር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም አርሶ አደሩ አላስፈላጊ የሆኑ ተባዮችን የመቆጣጠር ሥራ በንቃት እንዲያከናውኑ ተከታታይ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን በራስ አቅም ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ያሉት አቶ ለማ፥ ጫቶ በወረዳው አርሶአደሩ በምርት ዘመኑ በመኸር እርሻ የዘራቸውን ሰብሎች ከአረምና ተባይ መጠበቅና መከላከል ላይ ጊዜ ሳይሰጥ በትኩረት ሊሠራ ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
በመኸር እርሻ የተዘሩ ሰብሎችን ከአረምና ተባይ የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

More Stories
ብሄራዊ ቴያትር ከክልሉ 12 ዞኖች ለተውጣጡ ባለ ተሰጥኦዎች ምልመላ በአርባምንጭ ከተማ አካሄደ
ቀይ ባህርና አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ
በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ