በጎፋ ዞን ኢሲፔ ዲቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን ካፒታሉን 62 ሚሊየን ብር በማድረስ ዓመታዊ ትርፉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን አስታወቀ

ዩኒየኑ 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤሊያስ፤ ህብረት ሥራ ማህበራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለአርሶ አደሩ የተሻለ ትርፍ የሚያስገኙ የገበያ ትስስሮችን ከመዘርጋት ባለፈ የግብርና ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን ህገ ወጥ የዋጋ ንረትን ከማስተካከል አኳያ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለቸው ተናግረዋል።

የዞኑ ህብረት ሥራ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዲቻሳ፤ ዩኒየኑ በግል እና በመንግስት መካከል ያለውን የገበያ ጉድለት በመሙላት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

ዩኒየኑ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን በማፋጠን ሁለንታናዊ ብልጽግናኝ ለማረጋገጥ እየተጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የዩኒየኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ እስጢፋኖስ፤ ዩኒየኑ የግብርና ግብዓቶችን በማቅረብ ለምርታማነት ዕድገት የበኩሉን ድረሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን የማረጋጋት ስራ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ዩኒየኑ ካፒታሉን 62 ሚሊየን ብር በማድረስ ዓመታዊ ትርፉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን አስታወቀ።

የዞኑ ኅብረት ሥራ ልማት ጽህፈት ቤት ማህበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ደበበ፤ ዩኒየኑ መንግስት ባወጣቸው የህብረት ስራ ማህበራት የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያዎችን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረጉ ለውጤታማነቱ አበርክቶው የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

ለዩኒየኑ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ለውጤታማነቱ እየተጋ እንደሚገኝ የኑሩ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ብሩክ አባይነህ ገልጸዋል።

በጉባኤው የዩኒየኑ የፊዝካልና ፋይናንሻል ሪፖርት የሰባት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

የጉባኤው ተሳታፊዎችበበኩላቸው፤ ዩኒየኑ በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

ዩኒየኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት እውቅና ሰጥቷል።

ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን