የአየር ፀባይ መረጃ ስርጭት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ

የአየር ፀባይ መረጃ ስርጭት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ

ቦታ እና ወቅቶች ተኮር ብሔራዊ የአየር ፀባይ ትንቢያ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአርባ ምንጭ ተካሂዷል።

ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚያወጣቸው መረጃዎች ጉልህ ሚና እንዳለቸው ይታመናል።

ኢንስቲትዩቱ ቦታ ተኮር የሆኑ ትንበያዎችን በጥራት ተደራሽ ለማድረግ የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ገልጸዋል።

ወቅታዊ እና ተዓማኒ መረጃዎች ስርጭት በአየር ፀባይና ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመቋቋም የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ሰጪ እና ተቀባይ በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ዶ/ር አሳምነው አሳስበዋል።

የሲዳማ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚትዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ሀዋሳ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ከፍያለው አየለ በበኩላቸው፤ የሚትዎሮሎጂ አገልግሎቱን የስርጭት እና የመረጃ ጣቢያዎችን በእጥፍ ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

የምክክር መድረኩ ተሳታፊ እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር አበበ ከበደ፤ የአየር ፀባይ ስርጭት በፍጥነትና በጥራት ተደራሽ ማድረግ ለምርትና ምርታማነት ማደግ ጠቀሜታው የላቀ እንደሆነ አውስተው ህብረተሰቡ የመረጃ ልውውጡን ባህል እንዲያደርግም መክረዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያ ወ/ሪት ኤዴን አህመድን፤ ወቅታዊ የአየር ፀባይ ትንቢያ እና ስርጭት ከወቅቱ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ያግዛል ብለዋል።

በምክክር መድረኩ ሶስት የአየር ፀባይ ወቅቶችን መሠረት ያደረገ የአየር ሁኔታ ዳሰሳ ጥናት ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል።

ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን