አቶ ገላትያስ ሻሜ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

አቶ ገላትያስ ሻሜ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

የቴፒ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ አቶ ገላትያስ ሻሜ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾመዋል።

በምክር ቤቶች አሰራርና አባላት ሥነ ምግባርና ደንብ መሠረት መደበኛ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ በኋላ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ሲኖሩ አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በዚህም መነሻ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

የሸካ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ አቅራቢነት አቶ ገላትያስ ሻሜ የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው እንዲሾሙ ባቀረቡት መነሻ የምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ አጽድቀዋል።

ዘጋቢ: አስቻለው አየለ – ከማሻ ጣቢያችን