6ኛው የማህበረሰብ የምክክር ፎረም በይርጋጨፌ ከተማ እየተካሄደ ነው

6ኛው የማህበረሰብ የምክክር ፎረም በይርጋጨፌ ከተማ እየተካሄደ ነው

‎በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት “ለመቀናጀት እንወያይ፣ ለለውጥ እንሥራ” በሚል መሪ ቃል ነው ለስድስኛ ጊዜ የማህበረሰብ የምክክር ፎረም በይርጋጨፌ ከተማ እየተካሄደ ያለው።

‎በፎረሙ የፌደራልና የክልል ባለድርሻዎች እንዲሁም እህት ዩኒቨርሲቲዎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት እየተሳተፉ ሲሆን የማህበረሰብ አገልግሎት እና ጉድኝት ሥራዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የበለጠ በቅንጅት ለመስራት የሚደረግ ነው ተብሏል።

‎ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን