ትክክለኛ መረጃ በመሰብሰብ እና በማደራጀት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክ አገልግሎት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በአርባ ምንጭ ማዕከል ለ110 ሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየው የኢኮኖሚ ድርጅቶች የመስከ ቆጠራ ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡
በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ በክልሉ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለማካሔድ ለ25 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ስሜ አንበሴ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ማካሔድ ያሉንን የኢኮኖሚ አቅም በማወቅ ለመተንተንና ለሁለንተናዊ ኢኮኖሚ አቅም ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
ሰልጣኞች በ25 ቀናት ውስጥ የንድፈ ሐሳብና ተግባር ተኮር ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉንም ሀላፊው አስታውቀዋል።
የመረጃ ጥራትን በጠበቀ መልኩ ቆጠራው እንዲካሔድም ሀላፊው አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ ተከታታይነት ባለው ሁኔታ በሁሉም አቅሞች ዕድገት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸው ዘመናዊ የሆነ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ያሉንን አቅሞችን ለማወቅ እና ዕቅድ ዝግጅት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
የመረጃ ሰብሳቢዎች ትክክለኛ እና ተአማኒ መረጃ መሰብሰብ እንዲችሉ መክረዋል።
የጋሞ ዞን አስተዳደር ልዩ አማካሪ አቶ ደረጀ ጳውሎስ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለአጠቃላይ አገራዊ ዕድገት ወሳኝ በመሆናቸው በተደራጀ ሁኔታ የናሙና ቆጠራ በማድረግ የዕድገት ደረጃን ለመተንበይ ያግዛል ብለዋል።
ዘጋቢ ወ/ገብርኤል ላቀው ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በስልጤ ዞን የሚገኘው ሃይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 የትምህርት ዘመን በሃገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ውጤቱ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራን የማትጊያና የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ
የዋካ ቅርንጫፍ ጣቢያ ወቅታዊና ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ