ህዝብን በክብር ማገልገል የሀገር ወዳድነት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ተግባሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለጸ

ህዝብን በክብር ማገልገል የሀገር ወዳድነት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ተግባሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለጸ

ሀዋሳ፣ መስከረም 29/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህዝብን በክብር ማገልገል የሀገር ወዳድነት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ተግባሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ገለጸዋል።

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር  ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት  የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በመድረኩ ላይ ተገኝተው እንዳሉት የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን  ህዝብን ማገልገል የሀገር ወዳድነት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

ባለፈው በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በመንግስትና በከተማው ህዝብ ቅንጅት በርካታ የሰላምና የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው በተለይም ፈጣን ልማት እንዲሁም አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት  አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ከንቲባው ።

‎ፐብሊክ ሰርቫንቱ ለከተማዋ ሁለንተናዊ ልማትና ሰላም እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብር እያበረከተ ያለው  አስተዋጽኦ ማላቅ ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

‎የሚፈለገው ለውጥ ማምጣት የሚቻለው ሌብነትን የሚጠየፍ እንዲሁም ባህሉና ህዝቡን የሚያከብር አገልጋይ መፍጠር ሲቻል  መሆኑን ያነሱት አቶ ሙራድ ሁሉም ፐብሊክ ሰርቫንት በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ባለው አቅምና እውቀት ህዝቡን የሚመጥን ተግባር ለመፈፀም  መትጋት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የወልቂጤ ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በመገምገም  ከባለሙያ እስከ ተቋም ማበረታቻ መሰጠቱ በቀጣይ ለህዝቡ ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በተቋማትና በግለሰቦች ዘንድ መነሳሳት እንደሚፈጥር አስረድተዋል።

አያያዘውም  ሪፎርሙን በተግባር ይዘው የሰሩ ተቋማት የተሻለ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልፀው  ልምድ በመለዋወጥ  በ2018 በጀት አመት በሁሉም ተቋማት የተሻለ ተግባር ለማከናወን ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አሰተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ንቅበሸዋ መድረኩ በከተማው በ2017 በጀት አመት ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ውጤታማ የሆኑ  ተቋማት እና ፈጻሚዎች   ዕውቅና በመስጠት የውድድር መንፈስና ሥርዓት እንዲዘረጋ የሚያስችል መሆኑን አንስተው ጎን ለጎን ጉድለት ያለባቸው ራሳቸውን የሚፈትሹበት መድረክ እንደሆነ  አመላክተዋል።

የከተማው የመንግስት ሰራተኛ በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን በቅንነነትና በታማኝነት  ህዝብንና መንግስትን እንዲያገልግል በየተቋማቱ ልዩ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አቶ ግርማ አብራርተዋል።

በመድረኩ ላይ  አግኝተን  ያነጋርናቸው ተሳታፊዎች  በሰጡት አስተያየት ፐብሊክ ሰርቪስ እያደረገው ያለው ክትትልና ድጋፍ የተሻለ እንደሆነና  በተያዘው በጀት አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዕድል የሚፈጥር ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።

ከተማው  የሰላም ቀጠና ለማድረግ መንግስትና ህዝብ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል ።

በከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት አመት ሪፎርሙን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ዘጋቢ፦ ደጋጋ ሂሳቦ