በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰጠው  የአሰልጣኞች ስልጠና በኮሌጆች መካከል ልምድ ልውውጥ የተደረገበት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ

በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰጠው  የአሰልጣኞች ስልጠና በኮሌጆች መካከል ልምድ ልውውጥ የተደረገበት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት!” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ክላስተር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በማጠቃለያ መርሃ-ግብር የተገኙት በቢሮው የተቋማት አግባብነትና ጥራት ባለሙያ አቶ ሽመልስ ባትሳ ፤ ስልጠናው በኮሌጆች መካከል ልምድ ልውውጥ የተደረገበት ነው ብለዋል።

ስልጠናው በስምንት ትምህርት ክፍሎች ላይ ያተኮረና የአሰልጣኞችን የማሰልጠን አቅም ያዳበረ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰልጣኞች በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ላይ ግንዛቤ የፈጠረላቸው በመሆኑ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ማህበረሰቡ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመሰልጠን የተለያዩ የሙያ ባለቤት እንዲሆንም ጥሪ አስተላልፈዋል።

የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አንዱዓለም ገ/መድህን በበኩላቸው ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ልምድ ተግባራዊ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ማፍራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ሰልጣኝ መምህራንም ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የብቃት ምዘና በመዉሰድ የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ : ሀብታሙ ኃይሌ ከቦንጋ ጣቢያችን