የማህበረሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን በቀቤና ልዩ ወረዳና አጎራባች ቀጠናዎች ኮማንድ ፖስት አስታወቀ
በጉራጌ ዞን፣ በቀቤና ልዩ ወረዳና አጎራባች ቀጠናዎች የተሰሩ የኮማንድ ፖስቱ ስራዎች የሚመለከታቸው የፌደራል፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል።
በቀጠናው እስካሁን በኮማንድ ፖስቱ የተሰሩ ስራዎች ግምገማ ሪፖርት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ በአቶ ተመስገን ካሳ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
በመድረኩም ሜጀር ጀነራል አብድሮ ከድር፣ በተለያዩ የማዕረግ እርከን የሚገኙ የጦር መኮንኖች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ የጅማ፣ የምዕራብ ሸዋና የጉራጌ ዞኖች እንዲሁም የቀቤና ልዩ ወረዳ የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አዱኛ ትዛዙ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ