የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በክልሉ ያስገነባቸውን የማምረቻ ሼዶች ማስተላላለፍ የሚያስችል የውል ስምምነት ከባለሀብቶች እና ኢንተርፕራይዞች ጋር ተፈራረመ
ሀዋሳ: መስከረም 29/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በክልሉ ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን የማምረቻ ሼዶችን ማስተላላለፍ የሚያስችል የውል ስምምነት ከባለሀብቶች እና ኢንተርፕራይዞች ጋር ተፈራረመ።
በውል ስምምነት መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ናትናኤል ሚሊዮን ኮርፓሬሽኑ በ10 ከተሞች 15 ሳይቶችና ከ159 በላይ ሼዶችን አስገንብቶ እያስተዳደረ ይገኛል ብለዋል።
መድረኩ ኮርፓሬሽኑ በክልሉ ዘመናዊ፣ ምርታማ እና ተወዳዳሪ እንዱስትሪዎችን እየፈጠረ ያለ ተቋም መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው ።
ኮርፖሬሽኑ በተናጥል ሳይሆንበጋራ ክልሉን የኢንዱስትሪ ማእከል እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል ።
የዉል ስምምነቱ ከ6 ባለሀበቶች እና አምራች ኢንተርፕራዞች ጋር የተደረገ ሲሆን ስምምነቱም 9 ፋብሪካዎችንና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን መትከል የሚያስችል ነው ።
ዘጋቢ: እጸገነት ፈለቀ
More Stories
በስልጤ ዞን የሚገኘው ሃይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 የትምህርት ዘመን በሃገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ውጤቱ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራን የማትጊያና የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ
የዋካ ቅርንጫፍ ጣቢያ ወቅታዊና ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ