በእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ አራት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
የ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ 4 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ
በዚህ መሰረት ሊድስ ዩናይትድ ከቶትንሃም ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታል።
11 ሰዓት ላይ ደግሞ በለንደን ደርቢ አርሰናል በሜዳው ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር የሚያካሂደው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በሰሜን ለንደኑ ክለብ በአሰልጣኝነት 3ዐ0ኛ ጨዋታቸውን በዛሬው ዕለት ያከናውናሉ።
እንዲሁም የመስመር አጥቂው ቡካዮ ሳካ በመድፈኞቹ ቤት 200ኛ የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል።
በአሰልጣኝ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶ የሚመሩት መዶሻዎቹ ወደ ኤምሬትስ ስታዲየም አቅንተው ያከናወኗቸውን ያለፉትን 2 የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች በድል መወጣታቸው ይታወሳል።
በተመሳሳይ ሰዓት በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ማንቸስተር ዩናይትድ ከ8 ዓመታት ወደ ሊጉ ከተመለሰው ሰንደርላንድ ጋር ወሳኝ ፍልሚያ ያደርጋል።
በውጤት መጥፋት ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙት ሩበን አሞሪም በቀያዮቹ ቤት 50ኛ ጨዋታዎቸውን ዛሬ ያካሂዳሉ።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ በቼልሲ እና ሊቨርፑል መኻከል በስታንፎርድ ብሪጅ ይካሄዳል።
ሁለቱም ክለቦች በፕሪሚዬር ሊጉ ካጋጠማቸው ሽንፈት ለማገገም ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የሚመራው ቼልሲ የመጨረሻዎቹን 3 የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አለመቻሉ ይታወቃል።
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል እንዲሁ የዚህን ዓመት የመጀመሪያ ሽንፈቱን ባለፈው ሳምንት በክርስቲያል ፓላስ ማስተናገዱ አይዘነጋም።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የፕሪሚዬር ሊጉ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ እንደሚካሄዱ ተገለፀ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ሳውዲ ፕሮ ሊግ የማቅናት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ
የሰርከስ ስፖርት ሳይንሳዊ ጥበቡን ጠብቆ ለማጎልበት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ