የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በሣጃ ከተማ እየተከበረ ነው
ሄቦ ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሸጋገሪያ በዓል ነው።
የሄቦ በዓል የአዲስ ዓመት ብርሃን ማብሰሪያ፣ በተለያየ ምክንያት ከአካባቢው ርቀው የሚኖሩ ከቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር የሚገናኙበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ታላቅ በዓል ነው።
በሄቦ የዘመን መለወጫ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ኤርሲኖ አቡሬ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና የመንግስ ተጠሪና የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ አቶ ይሁን አሰፋ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ፣ በበዓሉ ላይ እየተሳተፉ ነው።
ከተለያዩ የክልሉ አከባቢዎችና ከሦስቱም የዞኑ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የብሔረሰቡ ተወላጆች፣ ባለሀብቶች፣ የትምህርት አመራሮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ ባለድርሻ አካላት እየሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
የተለያዩ የህክምና መድሀኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት መቻላቸውን በሚዛን አማን ከተማ በማህበረሰብ አቀፍ ፋርማሲ ሲገለገሉ ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገለፁ
በክረምት ወራት የታየውን ትጋት በበጋውም ለመድገም ቁርጠኞች መሆናቸውን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ
የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል የቋንቋና የባህል ሲንፖዚየም እየተካሄደ ነው