የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች እና በኣሪ ዞን ስር ባሉ መዋቅሮች የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች “ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦ ስትራቴጂ ቁመና” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ተወያዩ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች እና በኣሪ ዞን ስር ባሉ መዋቅሮች የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች “ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦ ስትራቴጂ ቁመና” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ተወያዩ

ሀዋሳ፡ መስከረም 21/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦ ስትራቴጂ ቁመና” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ በዚሁ መነሻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች እና በኣሪ ዞን ስር ባሉ መዋቅሮች የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች በተለያየ ቡድን ተከፋፍለው ተወያይተዋል።

መድረኩን የመሩ አካላትም ለተወያዮች በየመድረኮቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሀገር ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ አኳያ፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመገንዘብ የመንግስት ሠራተኞች በተሰማሩበት ቦታ ለእናት ሀገር ለውጥና ብልፅግና ተግተው መሥራት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

አሁን ላይ ያለው ሀገራዊ ሁኔታ ከመንግስት ሠራተኞች ልዩ ቁርጠኝነትና ትጋትን የሚጠይቅ መሆኑን መድረኩን የያዙ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ገልፀዋል።

በተለይ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስጠበቅ አኳያ ሁሉም የጠራ ግንዛቤ በመያዝ የሀገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ ከሁሉም የሚጠበቅ የዜግነት ሀላፊነት ነው ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ከቀረበው ሰነድ መነሻ የግልፀኝነት ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ምላሽ ተሰጥቶባቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ሁላችንም ለሀገራችን ለውጥና ሉዓላዊነት ጠንክረን እንሠራለን ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን